Monday, 31 July 2017



ዛሪ የምጽፈው አሉታዊ፡ ተቃራኒ ወይንም ትንሽን ድክመት አይደለም፤ ይሁን እና የተለመደውን የአስተሳሰብ መስተጋብር እና መስተጻምር ነው ለማሳየት ምሞክረው።


የፊት ፡ዘላለማዊ አለም ስለመኖሩ ብዙዎቻችን ብዙ ያልገባን ሰዎች እንዳለን የገባኝ የእለት ኑሮኣችን፡ ተራ የቀን ምሳችንን ማሸነፍ እንዳቃተን፡ የተረዳሁበት ወቅት ነበር።

እንደ ሃገር ሀገር ፡ሃገር ማለት መኖሪያ፡መመኪያ ፡ህይወትን ማስቀጠያ፡ዘር ሀረግን መተኪያ እንደሆነች ለመረዳት እንዲሁም መሆኑን ለመገንዘብ ማንም ተራ የሆነ ግለሰብ የሆነ ሰው  የሚያውቀው ጉዳይ ነው።

ነገርግን ይህ ሁሉ ሳይሆን ሲቀር እና ሃገር ማለት ፡ከወዲያወዲህ የለለ፡ያልተኖረ ልጅነትን ማሳለፊያ ፡ አ፟እምሮን ማዛጊያ፡ የለውጥ ጅምበርን እንደ ምጽአት ቀን መጠበቂያ፡ ተስፋን ተስፋ ማድረጊያ አቅም አልባ መሆኛ ከመሆንም አልፋ መኖር እና ያለመኖር ድምበር መለያው ከላ ተደበላልቆባት የዘጎቾን ህይወት ጎዳና ወይ በመኖር ወይ ባለመኖር ከፍላ ማሳየት ሲያቅታት ማየት በጣም ልብ የሚነካ ነው።

ዘጎቾ በስደት፡ ስራ በማጣት በሰሩትም ባመረቱትም ውጢት በማጣት፡ እላይ ታች ሲሉ ማየት እና በጣም እጅግ የተለመደ ከመሆኑም በላይ እንደ የትክክል ተግባር ማሳያ ውህደት የሚታይበት ወቅት ላይ ደርሰናል።

በርግጥ ሃገር ማለት ሰው ነው፡ ሰው ማለት ደግሞ የሚያስብ ጭንቅላት የተሰጠው ፡የሚያገናዝብ አእምሮ የተችረው ፍጡር መሆኑን ማንም ሰው ሆኖ የተፈጠረ ሰው የሚያውቀው እውነት ነው። እንግዲህ እዚህ ጋ ትልቁ ቁምነገር ሰው መሆኑን ማመኑን እና እንደ ሰው ምን ምን አይነት የማሰብ ሃላፊነት፡ድርሻ እንደተሰጠው ማወቁ ላይ ነው።

የአንዲት ሃገር የሰው ሁሉ  አእምሮ ከአምላክ በተሰጠው  እኩል የ አንጎል ቁርጥራጭ ጸጋ እኩል ቢሆንም ቅሉ፡ የሃገሪቱ ሰው ሁሉ አእምሮ በእኩል ፡ተመሳሳይ መልኩ ለሃገሪቱ በጎ አስተዋጾ እና የወደፊት ምሉህ አህጉራዊ አንጎል ማስቀጠያ ድልድይ በሁሉም  ዘጋ ይተገበራል ብሎ መጠበቅ ዘበት መሆኑ ግልብ ነው።

ታዲያ ይህን ሁሉ ለመወትወት ያበቃኝ ፡ የአንድ ወንድም አንገት መድፋት ፤በስነ ልቦና ቀውስ መታሰር፡  አለው የሚለው የገዛ የራሱ ማንነት ያለመሸነፍ ማስከበሪያ አቅም ማጣት፡ሰዎች በደረሰበት የክፋታቸውን ክርፋት የከረፉበት  ፡የት ወደቀ ወይስ ተነሳ ኧረ እንደውስ ይኖር ይሆን???  ብሎ እንኮዋን በዘመድ በሃገር ለተነፈገው፡የችግር ዲሪቶ ከመወለዱ አስቀድሞ አስቀድሞ እስከ አሁን ከጎለመሰበት ወቅት ድረስ እንደ ክፉ እርግማን ከስሩም ከላዩም መደቀን ልጅነቱን በወላጆቹ የድንቁርና አለም አልብሶ አእምሮው የትምህርት ና እውቀት  ጥማት ደብዝዞ ፡ በመሸሽ እና በስደት ካቲና አንጎሉን አሳምኖ ህይወቱን ለሚማስናት የወንድሚ የህይወት ታሪክከ ውስጥ ማንነቲ ያተሰማኝን ለመጻፍ ልቢ ከአ እምሮዪ ጋር በመጣመር የ እጆቺን አሻራ ለማሳረፍ የሞከርኩት።

ባለ ታሪኩ አብዱልከሪም ይባላል..............................................................................Yiketilal
Azar Kassa 29-7-2009 Asalla-Bale Robe




















No comments:

Post a Comment